የመቻሉ አጥቂ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶታል

በውድድር ዓመቱ አጋማሽ መቻልን የተቀላቀለው አጥቂ በዓለም ዋንጫ ማጣርያው ይሳተፋል።

የቶጎ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ቀናት ከደቡብ ሱዳን እና ዴሞክቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ጋር ላሉባት ሁለት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ስብስቧን ይፋ ስታደርግ በውድድር ዓመቱ አጋማሽ መቻል የተቀላቀለው አብዱ ሙታላቡ ኡታራ በዝርዝሩ ተካቷል።

በቅርቡ መቻልን ተቀላቅሎ በአምስት ጨዋታዎች ተሳትፎ 95 ደቂቃዎችን ሜዳ ላይ የቆየው ይህ ተጫዋች ቡድኑ ሀዋሳ ከተማን በረታበት ጨዋታ ወሳኝ የማሸነፍያ ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል።
ወደ መቻል ከማቅናቱ በፊት በሀገሩ ክለብ አስኮ ካራ እና በቡርኪና ፋሶው ሶናብል እንዲሁም በሳውዲ አረብያ ሁለተኛ የሊግ እርከን ተሳታፊ ለሆነው አል-ናይሪያ የተጫወተው አጥቂው በሀገሩ ቶጎ ማልያ አምስት ጨዋታዎች አከናውኖ አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል።