ሲዳማ ቡና በረከት አዲሱን ለሁለት አመት አገደ

የይርጋለሙ ክለብ ሲዳማ ቡና የፊት አጥቂው በረከት አዲሱ ላይ የሁለት አመት እገዳ መጣሉ ታውቋል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ባረጋገጠችው መረጃ መሰረት በረከት አዲሱ ለሌሎች የክለቡ ተጨዋቾች አርአያ የማይሆን የክለቡን ስምና ክብር የሚያጎድፍ ተግባር ሲፈፅም ደርሼበታለው በማለት ለሁለት አመት ምንም አይነት ግልጋሎት እንዳይሰጥ የዲሲፒሊን ቅጣት አስተላልፎበታል፡፡

ከእግር ኳስ ህይወቱ በስተጀርባ ከባድ ጉዳቶች እና ውዝግቦች የማያጡት የቀድሞው የንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ ከተማ አጥቂ ባለፈው የውድድር ዘመንም ከአሰልጣኙ ጋር በተፈጠረ ልዩነት ለክለቡ እምብዛም ግልጋሎት መስጠት አልቻለም ነበር፡፡

2 thoughts on “ሲዳማ ቡና በረከት አዲሱን ለሁለት አመት አገደ

  • January 13, 2017 at 3:36 pm
    Permalink

    ለምንተቀጣ የሚለው ዝርዝር ሁኔታ ባለመኖሩ መረጃውን ጎዶሎ አድርጎታል!!!!!!!!!!!!!

  • January 12, 2017 at 3:27 pm
    Permalink

    ልጁ ያጠፋዉ ጥፋት ለለሎች ማሰተማርያ ስለሚሆን ጥፋቶችን ግልፅ ቢታደርጉ ጥሩ ይሆናል ብዬ አምናለሁ!

Leave a Reply

error: