አሰልጣኝ ደረጄ በላይና ጅማ አባቡና ሊለያዩ?

ጅማ አባ ቡናን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳደጉት አሰልጣኝ ደረጄ በላይ ከክለቡ ሊለያዩ ከጫፍ መድረሳቸውን ከክለቡ አካባቢ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጅማ አባ ቡና ለመጀመርያ ጊዜ እየተሳተፈበት በሚገኝበት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደካማ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን አሰልጣኝ ደረጄ በላይም ከክለቡ ደጋፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ እየተነሳባቸው ይገኛል፡፡

የክለቡ አመራሮች ዛሬ ረፋድ በክለቡ ወቅታዊ የውጤት ቀውስ ዙርያ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን አሰልጣኝ ደረጄ በላይን እናሰናብት ወይስ እናቆይ በሚል ከብዙ ውይይት በኋላ አሰልጣኙ ክለቡ ካለበት የውጤት ቀውስ በፍጥነት እንዲመልሱ ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ክለቡ ለማሰናበት የሚገደድ መሆኑን የሚገልፅ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተለያይተዋል፡፡

ጅማ አባቡና የፊታችን እሁድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በሚያደርገው የ12ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የሚሸነፍ ከሆነ ምናልባትም አሰልጣኙ ሊሰናበቱ እንደሚችሉና ክለቡን በቀጣይነት የሚመሩ አሰልጣኞችን የመመልመል ስራ ከወዲሁ መጀመሩን ለማወቅ ችለናል፡፡

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ዜና ከክለቡ ደጋፊዎች በሚነሳባቸው ተቃውሞና ማስፈራርያ ምክንያት አንዳንድ ተጨዋቾች ለህይወታቸው በመስጋት ከክለቡ ለመልቀቅ ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡በድረገፁ የሚወጡ ፅሁፎች ምንጭ ካልጠቀስን በቀር ሙሉ ለሙሉ የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ ፅሁፎቹን ለራስዎ ፕሮግራም /ፅሁፍ ሲጠቀሙ ምንጭ ጠቅሰው ይጠቀሙ፡፡

2 thoughts on “አሰልጣኝ ደረጄ በላይና ጅማ አባቡና ሊለያዩ?

 • January 19, 2017 at 11:40 am
  Permalink

  በጣም ማዝነዉ አቶ ደረጀ ፕሪሚየር ሊግ ጫወታ አይተዉ አያቁም;; ለዛ ማሳያ የሰሩት ቡድን ነዉ ቡድኑ ለብሄራዊ ሊግ እንጂ ለፕሪሚየር ሊግ የማይመጥን ሆኖ ነዉ ያገኘሁት

 • January 19, 2017 at 11:18 am
  Permalink

  ለአሰልጣኝ ደረጀ ተጨማሪ የአንድ ጫወታ ዕድል መሰጠቱ አሳዝኖኛል መባረሩ ተገቢ ነዉ እላለሁ
  ምክንያቱም ከፋሲል አሰልጣን መማር አለበት

Leave a Reply

error: