ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች ሥልጠና ምዘና ውድድር ነገ ይጀምራል

በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አዘጋጅነት ከነሀሴ 13-27 በአዳማ የሚካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና የእግር ኳስ ውድድር በነገው ዕለት ይጀምራል። 

ከ13 በላይ በሆኑ የስፖርት ዓይነቶች የሚከናወነው ይህ ሀገር አቀፍ ታዳጊዎች ስልጠና ምዘና ውድድር እግር ኳስንም የሚያካትት እንደሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ኮሚቴ በማዋቀር  ከ8 የጨዋታ ታዛቢዎች እና 16 ዳኞች እንዲሁም ለውድድር  ከመጡ የሴትና ወንድ የክልል ከተማ አስተዳደር ቡድኖች አመራሮች ጋር በየባ ሆቴል ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ማድረጉን ለሚዲያ አካላት በላከው መግለጫ ላይ አስታውቋል። በስብሰባውም በውድድሩ ደንብ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በሁለቱም ፆታዎች የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት ተካሄዷል፡፡ በዚህም መሰረት ቡድኖቹ እንደሚከተለው ተደልድለዋል።

በወንዶች
ምድብ ሀ

አማራ 

ደቡብ 

ጋምቤላ

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ

ድሬዳዋ

ምድብ ለ

ሐረሪ

ኦሮሚያ

አዲስ አበባ

አፋር

በሴቶች

ምድብ ሀ

አዲስ አበባ

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ

አፋር

ደቡብ

ሐረሪ

ምድብ ለ

ኦሮሚያ

ጋምቤላ

አማራ

ድሬዳዋ


ነገ በውድድሩ መክፈቻ ቀን በወንዶች አዲስ አበባ ከኦሮሚያ አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በአዳማ ከተማ የሚገኘው ሱለይማን ሰሚድን የመሳሰሉ ተጨዋቾች የፈሩበት ይህ ውድድር ከዚህ ቀደም ለአምስት ጊዜያት የተካሄደ ሲሆን አምና በሀዋሳ ተስተናግዶ በወንዶች ቤኒሻንጉል ጉሙዝ  በሴቶች ደግሞ ደቡብ አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል።
* ፎቶዎች የአምና አሸናፊዎች እና የዛሬው ዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዐት።