ሴቶች ዝውውር | ንግድ ባንክ ሦስት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

ረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2010
ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ዝውውር እንቅስቃሴ የገባው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሷል።

በሴቶች እግርኳስ ስማቸው በግምባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው ብርቱካን ገብረ ክርስቶስ እንደ ሌሎች የቡድን አጋሮቿ ሁሉ ደደቢትን ለቃ ወደ ንግድ ባንክ አምርታለች። ሌላዋ የደደቢት ተጫዋች የነበረችው የቀኝ መስመር ተከላካይዋ ዘቢብ ገብረስላሴ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካይ ብዙዓየሁ ታደሰ ወደ ንግድ ባንክ ያመሩ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው።

ባንክ እስካሁን ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን የ9 ነባር ጫዋቾችንም ውል ማደስ ችሏል። ሰባት ተጫዋቾች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሲያራዝሙ አምበሏ ረሒማ ዘርጋው እና አጥቂዋ ሽታዬ ሲሳይ ዛሬ ውላቸውን ለተጨማሪ ዓመት ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው።