ኢትዮጵያ ቡና የቡሩንዲያዊውን አጥቂ ዝውውር አጠናቋል

ኢትዮጵያ ቡና የቡሩንዲ ዜግነት ያለው ሁሴን ሻባኒ የተባለ አጥቂ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል። 

ሁሴን ሻባኒ ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት የተስማማው ከሳምንት በፊት የውጪ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከመጠናቀቁ ቀደም ብሎ ሲሆን የህክምና ምርመራውን በስኬት ካጠናቀቀ በኋላ የአንድ ዓመት ኮንትራት መፈረሙ ታውቋል።

የ28 ዓመቱ ተጫዋች በሀገሩ ክለቦች ፍላምቤው እና ቪታል ኦ፣ በሩዋንዳዎቹ አማጋጁ እና ራዮን ስፖርትስ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካው ባርካ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ ጎል የማስቆጠር ከፍተኛ ችግር የተስተዋለበት ኢትዮጵያ ቡናን የፊት መስመር እንደሚያሻሽል ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *