የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች እሁድ ይደረጋሉ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች የ2011 የውድድር ዘመኑን ይቋጫል።

ካለፈለት ዓመታት በከፋ መልኩ በውዝግቦች እየተተራመሰ በሚገኘው ሊግ የመጨረሻው ሳምንት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ሁለቱ ቀደም ብለው አራት ሰዓት ላይ ሲደረጉ ቀሪዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ በተመሳሳይ 9:00 ይደረጋሉ።

ለዋንጫ እየተፋለሙ የሚገኙት ፋሲል ከነማ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ 9:00 የሚያደርጉት ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር ጨዋታ ሲጠበቅ ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ከመርሐ ግብር ማሟያነት እና ደረጃን ከማሻሻል የዘለለ ትርጉም የሌላቸው ናቸው።

ለጥያቄዎቹ ቀና ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ከሊጉ ራሱን ማግለሉን ያሳወቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወላይታ ድቻ ጋር 4:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም እንዲጫወት መርሐ ግብር ቢወጣለትም ክለቡ በአቋሙ ከፀና የመደረጉ ነገር አጠራጣሪ ነው። በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዋሎ በ28ኛ ሳምንት ያላከናወኑት ጨዋታ እጣ ፈንታ አስካሁን አልታወቀም።

የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይህንን ይመስላል

30ኛ ሳምንት
እሁድ ሰኔ 30 ቀን 2011
ሀዋሳ ከተማ 4:00
ደደቢት
ቅዱስ ጊዮርጊስ 4:00 ወላይታ ድቻ
ኢትዮጵያ ቡና 9:00 መከላከያ
ስሑል ሽረ 9:00 ፋሲል ከነማ
አዳማ ከተማ 9:00 ባህር ዳር ከተማ
መቐለ 70 እ. 9:00 ድሬዳዋ ከተማ
ሲዳማ ቡና 9:00 ወልዋሎ ዓ/ዩ
ጅማ አባ ጅፋር 9:00 ደቡብ ፖሊስ

ሙሉውን ይመልከቱ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: