U-20| ቅዱስ ጊዮርጊስ በማጠቃለያ ውድድሩ እንደማይሳተፍ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በነሐሴ ወር መጀመርያ እንደሚካሄድ ሲጠበቅ አንድ ቡድን በውድድሩ እንደማይሳተፍ አረጋግጧል።

ከየምድባቸው በዙር ውድድሩ ከ1-5 የወጡ በአጠቃላይ 10 ቡድኖችን የሚያሳትፈው የማጠቃለያ ውድድሩ በአዳማ ከተማ ከነሐሴ 5 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 19 እንደሚካሄድ ሲጠበቅ ከምድብ ሀ 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጨረሻው ሳምንት ከሀዋሳ ከተማ ባደረገው ጨዋታ ላይ እንዲሁም በፕሪምየር ሊጉ ዙርያ ባነሳው ቅሬታ ዙርያ እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን ጠቅሶ ከውድድሩ ማግለሉን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ቅዱስ ጊዮርጊስን ተክሎ የሚሳተፈው ቡድን በቀጣይ ጊዜያት የሚታወቅ ሲሆን ምናልባትም በምድብ ሀ 6ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ድሬዳዋ ከተማ ሊተካው የሚችል ቡድን ነው። ሆኖም የምስራቁ ክለብ ከለቀቃቸው ተጫዋቾች ጋር በተያያዘ በተጣለበት እገዳ ምክንያት መሳተፉ አጠራጣሪ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡