ሴቶች ዝውውር | አርባምንጭ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የነባሮችን ውል አራዝሟል

በሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን ተሳታፊ የሆነው አርባምንጭ ከተማ ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ሲያመጣ የአምስት ነባሮችን ውል አድሷል።

የአርምንጭ አዲስ ፈራሚዎች ቤተልሄም ብርሀኑ (አጥቂ ከጌዲኦ ዲላ)፣ መቅደስ ኃይሉ (አጥቂ ከሺንሺቾ ታዳጊዎች)፣ ማዕረግ ተስፋዬ (ተከላካይ ከሀዋሳ ከተማ)፣ መስከረም ኢሳይያስ (ተከላካይ ከድሬዳዋ ከተማ)፣ ርብቃ ጣሰው (ፎቶ ከላይ / ከሀዋሳ ከተማ ተከላካይ)፣ ሜሮን ዘሪሁን (አማካይ ከፋሲል ከነማ)፣ ዝናቧ አብጤ (አማካይ ከሀዋሳ ከተማ) ናቸው።

ከአዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ አምና ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ነባሮች ውል የታደሰ ሲሆን ሰርካለም ባሳ፣ ሰመወርቅ ጊፋዬ፣ ስንዱ ዳምጠው፣ ለምለም አስታጥቄ እና ድርሻዬ መንዛ ውል የተራዘመላቸው ተጫዋቾች ናቸው ፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: