ክለቦች የሴት እና የታዳጊ ቡድኖችን እንዲይዙ አስገዳጅ ህግ መውጣቱ ተገለፀ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዛሬው ዕለት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች የሴት እና የታዳጊዎች ቡድን እንዲይዙ አስገዳጅ ህግ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ማጠቃለያ ላይ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ዐወል አብዱራሂም በዘንድሮው የ2012 ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ ለሚሆኑ ክለቦች ጠንከር ያለ መመሪያን ፌዴሬሽኑ እንዳስቀመጠ ገልፀዋል፡፡ እንደ ም/ፕሬዝዳንቱ ገለፃ ሁሉም በፕሪምየር ሊግ ተካፋይ የሆኑ ክለቦች የሴቶች ቡድን እንዲያቋቋሙ፤ በወንዶች ደግሞ 15 እና 17 ዓመት በታች ቡድንን እንዲይዙ አስገዳጅ ህግ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህንንም ዘንድሮ ተግባራዊ ለማድረግ ፌዴሬሽኑ መዘጋጀቱንና ይህን ተፈፃሚ በማያደርጉት ላይ ጠንከር ያለ ውሳኔ ሊወስን እንደሚችል በማጠቃለያቸው ላይ ተናግረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ