የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 1 – 0 ስሑል ሽረ

መቐለ ስሑል ሽረን በኦኪኪ ኦፎላቢ ብቸኛ ግብ ካሸነፈ በኃላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች የሚከተለው አስተያየት ሰጥተዋል።

👉 ” ከሜዳችን ውጪ ያጣነውን ነጥብ እዚህ ለማካካት በማሰብ ነው የገባነው” ገ/መድህን ኃይሌ (መቐለ 70 እንደርታ)

ከሜዳችን ውጪ ያጣነው ነጥብ እዚህ ለማካካስ በማሰብ ነው የገባነው። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ገና በግዜ ያዩት ቀይ ካርድ የፈረጠው ነገር በዳኛው ላይ ጫና ፈጥሯል። በስርዓት እንዳይጫወቱ አርጓቸዋል። ቀዩ ትክክል ነው አይደለም የሚለውን ማንም ያየው ነው። ከዛ በላይ ግን ጨዋታውን መምራት ነበረበት። ወዳልተፈለገ አጨዋወት መግባት እና ሌሎች ነገሮች ነበሩ። መሀል ላይ የነበረው መቆራረጥ ጨዋታው በስርዓት እንዳይሄድ አድርጎታል በተወሰነ።

ከዕረፍት በኃላ በተቻለን መጠን የቁጥር ብልጫውን ተጠቅመን ለማጥቃት ነበር የገባነው።
ይዘነው የገባነው ታክቲክ ተጫዋቾቻችን አልተገበሩትም። ሆኖም ምንም እንኳ የተረጋጋ ነገር ባይኖርም አግብተን ጨዋታውን አሸንፈን ስለወጣን ለቀጣይ ትልቅ የሞራል ስንቅ ነው።

በአማካይ ክፍል ላይ ያለው ክፍተት

አዎ ክፍተቶች አሉ ። አንዳንዶቹ ባላቸው አቅም መጫወቱ ይችላሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ታክቲካሊ ዲስፕሊንድ አይደሉም። ችግሮቻችን አንድ ሁለት ብቻ ተብለው አያልቁም ብዙ ችግር አለብን። እስከ የውድድር ዓመቱ አጋማች ያሉንን ክፍተቶች አስተካክለን ለመጨረስ እንሞክራለን።

👉 “ዳኛው ጠቅላላ መንፈሱ ስለረበሸው እንዲህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም” ሳምሶን አየለ (ስሑል ሽረ)

ስለ ጨዋታው

የተጫወትነው ሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ ጋር ነው። በሜዳው እና ከደጋፊው ጋር እንደመጫወቱ መጠን ትንሽ ጠንካራ እንደሚሆን ገምተን ነበር። ነገር ግን ይዘነው የገባነው መንገድ መተግበር በማንችለበት ሁኔታ በተጀመረ በአስራ ሶስተኛ ደቂቃ ላይ ተጫዋቻችን በቀይ ካርድ በመውጣቱ የተለየ ነገር መስራት አልቻልንም። ዳኛው ጠቅላላ መንፈሱ ስለረበሸው እንዲ ነው ብሎ መናገር አይቻልም።

ስለ ቡድናቸው እንቅስቃሴ

የኛ ቡድ ጥሩ ነው። ከጨዋታ ጨዋታ ከፍተኛ መሻሻሎች አሉ። በጎዶሎ ተጫዋች ሆነን በመከላከል እና ክፍተት ባለመስጠት ለመጫወት ሞክረናል። እስከ ሰባ አምስተኛው ደቂቃ ድረስ ጥሩ ነበርን። ባለቀ ሰዓት በገባብን ጎል ነጥብ ጥለን እንድንወጣ አድርጎናል።

ስለ ቀይ ካርዱ

ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ዳኛው ሳያየው ረዳት ዳኛው በነገረው ነው።

© ሶከር ኢትዮጵያ