ከብራዚል በመጡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ነገ ሊሰጥ ነው

የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች ማኅበር ያዘጋጀው የአሰልጣኞች ስልጠና ነገ በሶሎት ሆቴል መሰጠት ይጀምራል።

ከብራዚል በመጡ ባለሙ አሰልጣኝ አርማንዲኒሆ በሚሰጠው በዚህ ስልጠና ለጊዜው የስልጠናው ትኩረቱን ያደረገው በአዲስ አበባ ለሚገኙ ከ17-20 ዓመት በታች ታዳጊዎች ላይ እየሰሩ የሚገኙ አሰልጣኞችን ነው። የኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ ተጫዋቾች ማኅበር ያዘጋጀው ይህ ስልጠና ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በሶሎት ሆቴል በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ትምህርቱ ይሰጥና ዓርብ የተግባር ትምህርቱ እና የስልጠናው የመዝጊያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ መጠናቀቂያው ይሆናል።

ይህን ስልጠና እንዳዘጋጀው ማኅበሩ ገለፃ ከሆነ በቀጣይ ተከታታይነት ያለው ስልጠናዎችን ከተለያዩ ሀገራት ጋር በመነጋገር ባለሙያዎችን በማስጠት ስልጠናውን ለመስጠት እንደታሰበ አሰልጣኝ እድሉ ደረጄ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል።

በዚህ ዓመት ብቻ የአሰልጣኞችን ሙያ ለማሻሻል በተለያዩ ተቋማት የተዘጋጁ የአሰልጣኞች ስልጠናዎች የተካሄዱ ሲሆን በቀጣይ እግርኳሱን ለማሳደግ መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ጠቋሚ ነው፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ