ፊሊፕ ኦቮኖ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል

የመቐለ 70 እንደርታው ግብ ጠባቂ ወደ ሀገሩ ተመልሷል

ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመታት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የተሳካ ቆይታ የነበረው እና ክለቡ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ በማስቻል ኮከብ ግብ ጠባቂ መሆን የቻለው ኢኳቶርያል ጊኒያዊ ግብ ጠባቂ ወደ ሀገሩ ክለብ ፊውቸር ኪንግስ ነው ያመራው። ኦቮኖ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት ለደቡብ አፍሪካው ኦርላንዶ ፓይሬትስ ጨምሮ ሶንይ ኤል ንጉማ እና ዲፖርቲቮ ሞንገሞ የተጫወተው ይህ ግብ ጠባቂ በብሔራዊ ቡድን ደረጃም የሀገሩ ቀዳሚ ተመራጭ መሆኑ ይታወቃል።

ከ2015 ጀምሮ ከሀገሩ ውጭ ላሉ ክለቦች የተጫወተው ይህ የ27 ዓመት ግብ ጠባቂ ከአምስት ዓመታት ቆይታ በኃላ ለፉትሮ ኪንግስ ፈርሞ ወደ ትውልድ ከተማው ሞንጎሞ ተመልሷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: