ሸገር ከተማዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለው የመስመር አጥቂ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።
አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን የቀጠሩትና ባለፉት ቀናቶች የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም የተጠመዱት ሸገር ከተማዎች አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በወልዋሎ ቆይታ የነበረው ቡልቻ ሹራን አስፈርመዋል። ባለፈው የውድድር ዓመት በወልዋሎ በነበረው ቆይታ በ26 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2145 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለገው ቡልቻ ከአዳማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በ2007 ላይ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ እስከ 2012 ድረስ አሳዳጊ ክለቡን በማገልገል ባለፉት ዓመታት በሰበታ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሲዳማ ቡና እና በወልዋሎ መጫወቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር በድጋሜ ለመስራት ወደ አዲስ አዳጊዎቹ ሸገር ከተማዎች አምርቷል።
