የዋልያዎቹ ረዳት አሰልጣኝ ታውቋዋል

የዋልያዎቹ ረዳት አሰልጣኝ ታውቋዋል

የዋልያዎቹ አለቃ መሳይ ተፈሪ ረዳት አሰልጣኝቸውን አሳውቀዋል።

በነሐሴ ወር መጨረሻ ከግብፅ እና ሴራሊዮን ጋር ለሚያከናውናቸው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ዝግጅታቸውን ነገ በአዳማ የሚጀምሩ ይሆናል።

ያለፈውን ዘጠኝ ወራት የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ረዳት በመሆን ያገለገሉት አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በቅርቡ የሀዋሳ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ በምትካቸው ሌላ ረዳት አሰልጣኝ ያፈላለጉት የዋልያዎቹ አለቃ በመጨረሻም ደጉ ዱባሞን ረዳታቸው እንዲሆኑ መምረጣቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ በእግር ኳስ ተጫዋችነት በስድስት ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፉ ሲሆን ወደ አሰልጣኝነቱ ከገባ በኋላ መተሀራ ቡድንን በመያዝ እስከ 2009 ድረስ ቆይታን ካደረጉ በኋላ በመቀጠል ከ2010 ጀምሮ በአዳማ ከተማ ረዳት እንዲሁም ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኖ ሲያገለግሉ ነበር። በማስከተልም በከፍተኛ ሊግ ሀምበሪቾ ዱራሜን በማሰልጠን ቡድኑን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማሳደጋቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮ ኤሌክትሪክ ረዳት አሰልጣኝ በመሆኑ እያገለገሉ ሲገኝ የአሰልጣኝ መሳይ ረዳት በመሆን መመረጣቸውን አውቀናል።