የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሊያደርግ ነው።
ከግብፅ እና ሴራሊዮን ጋር ለሚያደርጋቸው ሁለት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ዝግጅት የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቅርቡ ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ እንደሚያደርግ ታውቋል።
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የአቋም መለኪያው ጨዋታው እንዲዘጋጅላቸው ዕቅዳቸውንም አስገብተዋል። በዚህም መነሻነት እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ብሔራዊ ቡድኑ በቅርቡ ላለባቸው የአህጉራዊ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታዎች በዝግጅት ላይ ከሚገኙት ኢትዮጵያ መድን እና ወላይታ ድቻ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርግ ሲሆን ጨዋታዎቹ መቼ እና የት ቦታ እንደሚካሄዱ ግን አልተወሰነም።
ሶከር ኢትዮጵያ ጨዋታዎቹ መቼ እና የት ሜዳ እንደሚካሄድ ተከታትላ መረጃውን የምታቀርበው ይሆናል።