ሁለት ዓመት በዐፄዎቹ ቤት ቆይታ የነበረው ሁለገቡ ተጫዋች ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ተስማምቷል።
በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ እየተመሩ ዘግይተውም ቢሆን ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን እየፈፀሙ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች የታዳጊ ቡድን ፍሬያቸው የሆነውን ሁለገቡን ተከላካይ ኢዮብ ማቲያስን ለማስፈረም መስማማታቸው ታውቋል።
ከአዳማ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈው የመስመር ተከላካይ እና የመሐል ተከላካይ ሆኖ መጫወት የሚችለው ኢዮብ በዓፄዎቹ ቤት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ቆይታ ካደረገ በኋላ አሁን ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ተስማምቷል።