ጠንካራ ዝውውሮቸን እየፈፀመ የሚገኘው አዳማ ከተማ የሊጉን ዋንጫ ያነሳውን የመስመር አጥቂ የግሉ ለማድረግ ተቃርቧል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ቀድሞ ከሚታወቅበት ጠንካራ ተፎካካሪነት ተቀዛቅዞ ላለመውረድ ሲጫወት የቆየው አዳማ ከተማ ለ2018 የውድደር ዘመን ጠንካራ ቡድን ሆኖ ለመቅረብ በዝውውሩ በመሳተፍ የአምስት ተጫዋቾችን ዝውውር ማጠናቀቁ ይታወቃል። አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂውን አቡበከር ሳኒ ለማስፈረም መስማማቱ ታውቋል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው አቡበከር በመቀጠል በወልቂጤ ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ ነበር ኢትዮጰያ መድን የተቀላቀለው። የመስመር አጥቂው በተጠናቀቀው የውድደር ዘመን ለቡድኑ በ31 ጨዋታዎች 2683 ደቂቃዎች ላይ ተሳትፎ በማደረግ ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ኢትዮጵያ መድን የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ የራሱን አስቶዋፆ አድርጓል። አቡበከርም በቀጣይ ለሁት ዓመት የሚያቆይ ውል ከአዲሱ ቡድኑ ጋር አስሯል።