በድሬደዋ ከተማ ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂ አሁን መዳረሻው አዲስ አዳጊው ክለብ ሆኗል።
ያልተጠበቁ ዝውውሮችን እየፈፀሙ ያሉት አዲስ አዳጊዎቹ ነገሌ አርሲዎች የዳዊት ተፈራን እና የናትናኤል ሰለሞንን ዝውውር ካጠናቀቁ በኋላ በመቀጠል ሦስተኛ ፈራሚያቸው የመስመር አጥቂው ሀቢብ ከማል ሆኗል።
የመስመር አጥቂው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ በኮልፌ ቀራንዮ እንዲሁም አርባ ምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን መጫወት የቻለው ሲሆን ያለፉትን ስድስት ወራት በድሬዳዋ ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ በስምምነት በመለያየት አሁን ማረፊያው ነገሌ አርሲ ሆኗል።
