ከነገው መሳኝ ጨዋታ አስቀድሞ የሉሲዎቹ አንበል ሎዛ አበራ አስተያየቷን ሰጥታለች

ከነገው መሳኝ ጨዋታ አስቀድሞ የሉሲዎቹ አንበል ሎዛ አበራ አስተያየቷን ሰጥታለች

👉 “በ90 ደቂቃ ውስጥ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን”

👉 “ሁላችንም በተሻለ ስነልቦና ላይ ነን”

👉 “በእርኳስ ምንም ነገር ማድረግ ይቻላል” ሎዛ አበራ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2026 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ለማለፍ የመጀመርያ ጨዋታቸውን ከታንዛንያ ጋር አድርጎ በሁለት ለዜሮ ሽንፈት በመመለስ ወሳኙን የመልስ ጨዋታውን ነገ ከማድረጉ አስቀድሞ አንበሏ ሎዛ አበራ የመጀመርያው ጨዋታ አለመኖሯን እና ለመልሱ ጨዋታ ታሪክ ለመስራት ማሰቧን ተጠይቃ ተከታዮን አስተያየቷን ሰጥታለች።

“የመጀመሪያው ጨዋታ ላይ ያልመጣሁት የፊፋ የውድድር ጊዜ October 20 / ጥቅምት 10 ነበር የሚከፈተው ክለባችን ደግሞ ጨዋታ ስለነበረው እኔን መልቀቅ እንደማይችል ለፌዴሬሽን አሳውቋል። ለሁሉም ማሳወቅ የምፈልገው እኛ ክለብ ውስጥ እኔ ብቻ ሳልሆን አምስት የምንሆን የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች አለን እና ሁላችንም በዛው ቀን October 20 / ጥቅምት 10 ነው የተለቀቅነው ፤ ጨዋታችንም October 19/ጥቅምት 9 ስለነበር ያንን ማድረግ አልቻልኩም። ሳልናገር ማላልፈው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በቶሎ መጥቼ ቡድኑን እንድቀላቀል ብዙ ጥረት አድርጓል። ከገባሁበት ጊዜ ጀምሮ ብሔራዊ ቡድን ከታንዛኒያ እስኪመለስ ሁለት ቀን ልምምድ በግሌ ሠርቻለሁ። ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፍን ብዙ ዓመታት ሆኖታል እኔም ያንን አላሳካሁም ወይም የእኔ ትውልድ አላሳካም። በምንችለው አቅም ያለንን ሁሉ ሰጥተን ውጤቱን ቀልብሰን ከእግዚአብሔር ጋር ታሪክ እንደምንሠራ አምናለሁ። ሁሉም ልጆች ውስጥ ያለውን ይሄንን ነው። የድሬዳዋም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደየሃይማኖቱ እንዲጸልይልን እና እንዲደግፈን እጠይቃለሁ።”

“በስነ ልቦናው ምን ያህል ተዘጋጅታችኋል ለሚለው ባለፈው ዩጋንዳ ላይ ተሸንፈን እዚህ ቀልብሰን አሸንፈን አልፈናል እና ያም ጥሩ መንፈስ ይሰጠናል። በ90 ደቂቃ ውስጥ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። በተሻለ ስነልቦና ላይ ነን ሁላችንም። በእግርኳስ ምንም ማድረግ ይቻላል” ብላለች።