አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ ቅጣት ተላልፎበታል

አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ ቅጣት ተላልፎበታል

የብርቱካናማዎቹ አሰልጣኝ እና የሽረ ምድረገነቱ ወሳኝ ተጫዋች ከአወዳዳሪው አካል ከበድ ያለ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

የ26ኛ ሳምንት ኮሚዩኒኬ ይፋ ያደረገው የሊጉ አክሲዮን ማኅበር ከድሬዳዋ ከተማ እና ስሑል ሽረ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ወደ መልበሻ ክፍል መሄጃ ኮሪደር ላይ ለተፈጠረ ግርግር መነሻ ያላቸውን የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን ቅጣት ጥሎባቸዋል።

አሰልጣኙ የስድስት ጨዋታ እና የ20ሺህ ብር ቅጣት ሲተላለፍባቸው በሊጉ ለመቆየት በሚደረገው ትግል ውስጥ እጅግ ወሳኝ የሆኑትን እነዚሁ መርሐግብሮች የማይመሩ ይሆናል።

* አሰልጣኙ ባለፈው ዓመት በ25ኛ ሳምንት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በተደረገ ጨዋታ በጨዋታው ላይ ለተመለከቱት ቀይ ካርድ 3 ጨዋታ ፤ የጨዋታ አመራሮችን አጸያፊ ስድብ በመሳደብ በሚል 6 ጨዋታ በአጠቃላይ 9 ጨዋታዎችን ተቀጥተው እንደነበር ይታወሳል።

– ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ እንደ አሰልጣኙ በተመሳሳይ ወደ መልበሻ ክፍል መግቢያ ኮሪደር ላይ ለተፈጠረ ረብሻ መነሻ የተባለው የሽረ ምድረገነቱ ወሳኝ ተጫዋች ሽመክት ጉግሳ በተመሳሳይ የ6 ጨዋታዎች እና የ20ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል።