ለ25 ዓመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ የዳኝነት ዓለም ውስጥ ያገለገሉት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኃይለኢየሱስ ባዘዘው (ዶ/ር) ከዳኝነት ሙያ ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ አደረጉ።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ ሦስት ጊዜ “የዓመቱ ምስጉን ዳኛ” ተብለው በመመረጥ ብቸኛው ግለሰብ መሆን የቻሉት ዶ/ር ኃይለኢየሱስ ከሩብ ክፍለ ዘመን ቆይታ በኋላ ዳኝነት ማቆማቸውን ገልጸዋል። ዳኛው በስንብት ንግግራቸው ለስኬታቸው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በሙሉ ያመሰገኑ ሲሆን በቀጣይም በክልል ደረጃ ሆነ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ በሙያቸው ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ዶ/ር ኃይለኢየሱስ አሁን ላይ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

