ሪፖርት| ኢትዮጵያ መድን ወደ ግማሽ ፍፃሜ የተሸጋገረ ሦስተኛው ክለብ ሆኗል

ሪፖርት| ኢትዮጵያ መድን ወደ ግማሽ ፍፃሜ የተሸጋገረ ሦስተኛው ክለብ ሆኗል

ኢትዮጵያ መድኖች ከዕረፍት በፊት ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ቤንችማጂ ቡናን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ መቀላቀል ችለዋል

በአጋማሹ ጥሩ መንቀሳቀስ የቻሉት የኢትዮጵያ መድኖች 25ኛው ደቂቃ ላይ በሜዳው የግራ መስመር ረመዳን የሱፍ ይዞ ገብቶ በጥሩ ሁኔታ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ሳሙኤል ሳሊሶ በአየር ላይ እንዳለ በእግሩ መትቶ በማስቆጠር ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።

ከአስር ደቂቃዎች በኋላ የመጀመሪያው ግብ ባለቤት የሆነው ሳሙኤል ሳሊሶ ከማዕዘን ምት ያሻማውን ኳስ የቡድኑ አዲስ ፈራሚ ቤንጃሚን ኮቴ 35ኛው ደቂቃ ላይ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር ቡድኑን ሁለት ለዜሮ እየመራ ወደ ዕረፍት እንዲያመራ አድርጓል።

ከዕረፍት መልስ ቤንች ሚጂዎች ጥሩ መንቀሳቀስ የቻሉ ቢሆንም ነገር ግን ኢትዮጵያ መድኖች የተጫዋች ለውጥ በማድረግ ጨዋታውን መቆጣጠር ችለዋል። በዚህም በረመዳን የሱፍ እና ተቀይሮ በገባው አማኑኤል ኤርቦ ሙከራዎች ለግብ የቀረቡ ቢሆንም ተጨማሪ ግቦችን ሳያስቆጥሩ ጨዋታው ሁለት ለዜሮ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።