የደቡብ ሱዳን ፕሪምየር ሊግ ክለብ ጃሙስ እያሰለጠኑ የሚገኙት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከክለቡ ጋር ሳይለያዩ እንዳልቀረ እየተሰማ ይገኛል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በተለያዩ ሀገር ውስጥ በአፍሪካ ሀገራትም በማሰልጠን የሚታወቁት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከወራት በፊት የደቡብ ሱዳን ክለብ የሆነውን ጃሙስን ለሦስት ዓመት ቆይታ ለማሰልጠን ተስማምተው ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር በማቅናት እያሰለጠኑ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ሆኖም ግን ከቅርብ ቀናት ወዲህ የተለያዮ የደቡብ ስዳን መገናኛ ቡዙሀን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና በክለቡ አመራሮች መካከል ከውጤት ማጣት ጋር በተያያዘ በመሀከላቸው ንፋስ እንደገባ እና ሊለያዮ የሚችሉበት ዕድሎች ሰፊ መሆናቸውን ከተለያዮ ምንጮች በማረጋገጥ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ቆይተዋል።

ሶከር ኢትዮጵያም ዛሬ ባደረገችው ማጣራት በአሁን ሰዓት የሁለት ሳምንት ጨዋታዎች በቀሩት የደቡብ ሱዳን ሊግ ትናት ጃሞስ ባደረገው ልምምድ አሰልጣኝ ውበቱ እንደ ወትሮ ሳየሰሩ እንደቀሩ እና ቡድኑ በጊዜአዊ አሰልጣኝ እየተመራ ልምምዳቸውን ሲያከናውኑ እንደነበረ ከመረጃ ምንጫችን አረጋግጠናል።
ይህን ተከትሎ ምንም እንኳን ክለቡ እስካሁን ይፋዊ በሆነ መንገድ በሁለቱ መካከል መለያየታቸውን ባያረጋግጥም ቡድኑ ሁለት ቀሪ ጨዋታዎቹን በጊዛዊ አሰልጣኝ እየተመራ እንደሚጫወት እና አሰልጣኝ ውበቱ እና የአሰልጣኝ አባሎቶቻቸው ከክለቡ ጋር የመለያየታቸው ነገር እርግጥ ሳይሆን አይቀርም።
በዚህ ጉዳይ የሚኖር አዳዲስ ነገርሮች ካሉ በቀጣይ የምንመለስበት ይሆናል።

