ንግድ ባንክ ቡድኑን ማጠናከሩን ቀጥሏል

ንግድ ባንክ ቡድኑን ማጠናከሩን ቀጥሏል

ቻምፒዮኖቹ ግብ ጠባቂ አስፈርመዋል።

በተከታታይ ለ6ኛ ጊዜ እንዲሁም በአጠቃላይ ለ9ኛ ጊዜ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴካፋ ቻምፒዮንስ ሊግ ለሚጠብቀው ውድድር ይረዳው ዘንድ ቡድኑን ማደራጀቱን የቀጠለ ሲሆን የአራት ተጫዋቾቹን ውል ካደሰ በኋላ ወደ ዝውውሩ በመግባት ግብ ጠባቂ ማስፈረሙ ታውቋል።

ቡድኑን የተቀላቀለችው ግብ ጠባቂዋ ገነት ኤርሚያስ ናት። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከባሕር ዳር ከተማ ጋር ቆይታ የነበራት ቁመታሟ ግብ ጠባቂ ገነት በሐምራዊ ለባሾቹ ቤት ለመጫወት ፊርማዋን አኑራለች።