የመቻል ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት ውበቱ አባተ ረዳቶቻቸውን አሳውቀዋል።

ለ2019 የውድድር ዘመን ጠንካራ ቡደን ለመገንባት እንቅስቃሴ የጀመሩት መቻሎች አዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማምተው የነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም መስማማታቸውን ስናደርሳቹሁ ቆይተናል። አሁን ደግሞ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አብረዋቸው የሚሰሩትን ምክትሎቻቸውን መሾማቸውን አውቀናል።
አሰልጣኝ ሲሳይ ከበደ የመቻል ረዳት አሰልጣኝ ለመሆን ተሹመዋል። አሰልጣኝ ሲሳይ በተጫዋችነት በአሰልጣኝነት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ረጅም አመት ያገለገለ ሲሆን በ2016 ንግድ ባንክ ቻምፒዮን ሲሆን የቡድኑ ረዳት አሰልጣኝ ነበር። አሁን የአሰልጣኝ ውበቱ ረዳት መሆኑ ታውቋል።
በግብጠባቂ አሰልጣኝነት አዳሙ ኑሩ ውላቸውን በማራዘም ከአሰልጣኝ ውበቱ ጋር የሚቀጥሉ ሲሆን በዳሽን ቢራ፣ በሀዋሳ ከተማ፣ በሰበታ ከተማ ጋር ሲሰሩ የቆዮ ሲሆን አሁን ለተጨማሪ ዓመት ከመቻል ጋር የሚቆዮበትን ውል አራዝመዋል።

