ከድሬደዋ ከተማ ጋር በግሉ ጥሩ ቆይታ የነበረው የግራ መስመር ተከላካይ ወደ ቡናዎቹ ያመራ ሦስተኛ ተጫዋች ሆኗል።

ለ2019 የውድድር ዘመን ጠንካራ ቡድን ለመገንባት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች የግብዘቡን አቡበከር ኑራን እና የተከላካይ በረከት ወልደዩሐንስን ዝውውር ለማጠናቀቅ መስማማታቸው ይታወቃል። አሁን ስሙ ከተለያዮ ክለቦች ጋር ሲነሳ የሰነበተው የግራ መስመር ተከላካይ አብዱልሰላም የሱፍ የቡናማዎቹ ሦስተኛ ፈራሚ ለመሆን መስማማቱን አውቀናል።
የእግርኳስ መነሻውን ቤኒሻንኩል ከተማ አድርጎ በሀምበሪቾ ቆይታ ካደረገ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በድሬደዋ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን አሁን መዳረሻው ቡናማዎቹ ሆኗል።

