የ2017 የሊጉ አሸናፊ የነበረው ኢትዮጵያ መድን የመጀመርያ ፈራሚውን ለማግኘት ተስማምቷል።

በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚመራው ኢትዮጵያ መድን ዘግይቶም ቢሆን ወደ ዝውውሩ በመግባት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ቆይታ የነበረውን አቡበከር ሻሚል የመጀመርያ ፈራሚው ለማድረግ መስማማቱ አውቀናል።
ከዚህ ቀደም ለኮልፌ እና ለአዳማ ከተማ ተጫወቶ ያሳለፈው አማካዩ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ለድሬዳዋ ከተማ የተጫወተ ሲሆን አሁን መዳረሻውን ኢትዮጵያ መድን ለማድረግ ተስማምቷል።

