አሸናፊ ሀፍቱ አዲስ ክለብ አግኝቷል

አሸናፊ ሀፍቱ አዲስ ክለብ አግኝቷል

በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ተጫዋች አዲስ ክለብ አግኝቷል።

ከመቐለ 70 እንደርታ ሁለተኛ ቡድን ተገኝቶ ላለፉት ዓመታት ቡድኑን በማገልገል ላይ የቆየው እና በ2011 ከአሳዳጊ ክለቡ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያሳካው በመስመር ተጫዋችነት እና በመስመር ተከላካይነት መሰለፍ የሚችለው ሁለገቡ አሸናፊ ሀፍቱ የኢትዮጵያ መድን የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሁለተኛ ፈራሚ ሆኖ ቡድኑን ተቀላቅሏል።

በ2015 ዓ.ም ለስድስት ወራት ከተጫወተበት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ የእግር ኳስ ሕይወቱን በሙሉ በመቐለ 70 እንደርታ ያሳለፈው አሸናፊ ከአቡበከር ሻሚል ቀጥሎ ኢትዮጵያ መድንን የተቀላቀለ ሁለተኛ ፈራሚ ሆኗል።