አዲስ አዳጊዎቹ ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል

ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ባሳደገው አሰልጣኝ በሽር አብደላ እየተመሩ የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ለ2019 የውድድር ዓመት ራሳቸውን አጠናክረው ለመቅረብ በእንቅስቃሴ ላይ ያሉት ሀላባ ከተማዎች አሁን ደግሞ ወጣት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። ቡድኑን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ተጫዋች ደግሞ ቤኒናዊው ራያን ሊሳሲ ነው ፤ 21 ዓመት ዕድሜ ያለው ግብ ጠባቂው ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀገሩ ክለብ ኮተን ስፖርት ቆይታ ያደረገ ሲሆን በቤኒን ቻምፕዮን ሺፕ ጥሩ ብቃት በማሳየት ተስፋ ከሚደረግላቸው ወጣት ግብ ጠባቂዎች አንዱ ነው።

