‘የሃላ ኢንድ’ ፍሬ ቃለአብ ሜሮን አዲስ ክለብ አገኘ

‘የሃላ ኢንድ’ ፍሬ ቃለአብ ሜሮን አዲስ ክለብ አገኘ

በቅርቡ ከመድፈኞቹ ጋር የተለያየው ወጣቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወደ ስዋንሲ አምርቷል።

ከጥቂት ዓመታት በፊት በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እና በአርሰናል ወጣት ቡድኖች ላይ ባሳዩት ብቃት የብዙዎች ትኩረት ስበው የነበሩት መንትዮቹ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቃለአብ ሜሮን እና የአብስራ ሜሮን ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ በአስራ ስድስት ዓመታቸው ከእናት ክለባቸው አርሰናል ጋር መለያየታቸው ይታወሳል።

በ2022/23 የውድድር ዓመት ከአርሰናል ታዳጊ ቡድኑ ጋር ‘የናሽናል ካፕ’ አሸናፊ የነበሩት ወንድማማቾቹ ከታዳጊ ቡድኑ ከተለያዩ በኋላ በዋነኝነት መስመር ተከላካይነት እንዲሁም በመስመር ተጫዋችነት ማገልገል የሚችለው የአብስራ ሜሮን ከሳምንታት በፊት የባየርን ሚዩኒክ ግሎባል ስኳድን ተቀላቅሎ ቆይታ እያደረገ ሲገኝ የመስመር ተጫዋቹ ቃለአብ ሜሮን ደግሞ በትናንትናው ዕለት በይፋ የዌልሱ ክለብ ስዋንሲ የታዳጊ ቡድንን ተቀላቅሏል።