ኢትዮጵያ መድን የዋንጫ ቱትን ውል አራዝሟል

ኢትዮጵያ መድን የዋንጫ ቱትን ውል አራዝሟል

ከትናንት በስቲያ ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ መድኖች የታዳጊ ቡድን ፍሬያቸውን ተጫዋቾች ውል አራዝመዋል።

በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የሚመራው የ2017 የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ወደ ዝውውሩ በመግባት ገለታ ሀይሉ፣ ከማል ሀጂ፣ አቡበከር ሻሚል እና አሸናፊ ሀፍቱን በማስፈረም የእስማኤል አብዱል ጋኒዩ ውል ማራዘማቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ የመሀል ተከላካዩን ዋንጫ ቱትን ውል ማራዘማቸው ታውቋል

ከጋምቤላ ምድር የፈለቀው ዋንጫ በኢትዮጵያ መድን ታዳጊ ቡድን ባደረገው ድንቅ ቆይታ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እያደረገ የቆየ ሲሆን አሁን ባሳዳጊው ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙን ሰምተናል።