ይገዙ ቦጋለ ወደ አሳዳጊው ተመለሰ

ይገዙ ቦጋለ ወደ አሳዳጊው ተመለሰ

በተጠናቀቀው ዓመት ከአዞዎቹ ጋር ያሳለፈው አጥቂ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ እናት ክለቡ ተመለሰ

በተጠናቀቀው ዓመት በአርባምንጭ ከተማ ቆይታ ያደረገው አጥቂው ይገዙ ቦጋለ ከአንድ ዓመት የአዞዎቹ ቆይታ በኋላ ወደ እናት ክለቡ ሲዳማ ቡና ተመልሷል።  በ2014 ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የነበረው አጥቂው ከሲዳማ ቡና ታዳጊ ቡድን ካደገ በኋላ በዋናው ቡድን ለስድስት ዓመታት ያገለገለ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአንድ ዓመት የአርባምንጭ ከተማ ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ሲዳማ ቡና ተመልሷል።

የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም ወደ ክረምቱ  የዝውውር መስኮት ከገቡ በኋላ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ስብስቡ በመቀላቀል ለአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ በመዘጋጀት ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ከቀናት በፊት ዝግጅት መጀመራቸው ይታወሳል።