ዩጋንዳዊው ወደ ሲዳማ ቡናን ለማቅናት ተስማማ

ዩጋንዳዊው ወደ ሲዳማ ቡናን ለማቅናት ተስማማ

በሲንጋዳ ብላክ ስታርስ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ቻምፕዮኖቹን ለመቀላቀል ተስማማ

በዝውውር መስኮቱ የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ለሚጠቃቸው የካፍ ቻምፕዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪየ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅታቸውን በማድረግ ላይ የሚገኙት እና ቀድም ብለው ሴኔጋላዊውን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ ዩጋንዳዊው ካሊድ አውቾ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ላለፉት ዓመታት በሲንጋዳ ብላክ ስታርስ ሲጫወት የቆየው የተከላካይ አማካዩ ከዚህ ቀደም በያንጋ አፍሪካንስ ፣ ምስር አል መቃሳ ፣ ሲምባ ፣ ጎር መሀያ እንዲሁም በሰርብያ ክለቦች ሬድ ስታር እና ኦ ኤፍ ኬ ብዮጋርድ ተጫውቶ በክለብ ደረጃ አምስት የሊግ ዋንጫዎች ጨምሮ በድምሩ አስራ ሁለት ዋንጫዎች ማንሳት ችሏል። የኬንያና ዩጋንዳ ጥምር ዜግነት ያለው እና ለዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን 78 ጨዋታዎች በማድረግ በሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች መሳተፍ የቻለው ይህ ተጫዋች ለረዥም ዓመታት ሀገሩን በአምበልነት ማገልገልም ችሏል።