አስቻለው ታመነ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

አስቻለው ታመነ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

ሁለት ጊዜ የሊጉ ኮከብ ተጫዋችነትን ክብር ያገኘው አስቻለው ታመነ ከብርቱካናማዎቹ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል

በቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ከታዩ ምርጥ ተከላካዮች መካከል አንዱ የሆነው እና ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተሸለመው አስቻለው ታመነ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው ዛሬ ከድሬደዋ ከተማ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት የመራው ተከላካዩ ከዚህ ቀድም በዲላ ከተማ ፣ ደደቢት ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ፋሲል ከተማ በተጠናቀቀው ዓመት ደግሞ በድሬደዋ ከተማ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ
ከቡድኑ ጋር ቀሪ ውል እያለው በስምምነት መለያየቱ እርግጥ ሆኗል።