ያለፈውን አንድ ዓመት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ ያደረገው አሚኑ ነስሩ ውሉን አራዝሟል።

ከፈረሰኞቹ ጋር እንዳማይቆይ ሲነገር የነበረው እና ወደ ሌሎች ክለቦች ሊያመራ እንደሚችል የተጠበቀው ተከላካዩ አሚኑ ነስሩ ውሉን ለማራዘም መስማማቱ ታውቋል።
በከፍተኛ ሊጉ በሀላባ ከተማ ባሳየው ጥሩ ጊዜ በተጠናቀቀው ዓመት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጣው አሚኑ ከዚህ ቀደም በመቐለ ሰባ እንድርታ እና ጅማ አባ ጅፋር በመጫወት የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወቃል።

