የወቅቱ የሊጉ ኮከብ በሲዳማ ቡና ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል

የወቅቱ የሊጉ ኮከብ በሲዳማ ቡና ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል

ከሳምንታት በፊት አስቀድመን በነገርናችሁ መረጃ መሠረት ያሬድ ባየህ በሲዳማ ቡና ለመቆየት ተስማምቷል።

ያለፉትን ዓመታት በወጥነት በምርጥ አቋም ከተመለከትናቸው ተከላካዮች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው እና ከሁለት ቡድኖች ጋር የሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ያነሳው የ2018 የሊጉ ኮከብ ተጫዋችነትን ክብር ያገኘው የኋላው ደጀን ያሬድ ባየህ ከሲዳማ ቡና ጋር ለተጨማሪ ዓመት ውሉን ለማራዘም መስማማቱን አስቀድመን ነግረናችሁ ነበር።

በመሆኑም ዛሬ በይፋ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ለሁለት ዓመት ከሲዳማ ቡና ጋር አብሮ የሚቆይበትን ፊርማውን ማኖሩን አውቀናል።