ወሳኙ አጥቂ በሲዳማ ቡና ይቆያል

ወሳኙ አጥቂ በሲዳማ ቡና ይቆያል

ከሳምንታት በፊት በሲዳማ ውሉን ለማራዘም የተስማማው መስፍን ታፈሰ ዛሬ በይፋ ፊርማውን አኑሯል።

ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን የተገኘው እና በኢትዮጵያ ቡና ከተጫወተ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሲዳማ ቡና ጋር ድንቅ ዓመታትን እያሳለፈ ያለው ፈጣኑ የመስመር አጥቂ መስፍን ታፈሰ ውሉን ለማራዘም መስማማቱን ከሳምንት በፊት ነግረናችሁ ነበር።

አሁን በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ለሁለት ዓመት በሲዳማ ቡና ለመቆየት ውሉን በፊርማ ማሰሩን አውቀናል። ሲዳማ ቡና ወሳኝ ተጫዋቾቹን ያሬድ ባየህን እና መስፍን ታፈሰን ማቆየት መቻሉ ለቡድኑ እፎይታ የሚሰጥ ነው።