አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሽልማት ተበረከተላቸው

አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሽልማት ተበረከተላቸው

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ፈረሰኞቹን ያሰለጠኑት የወቅቱ የአዳማ ከተማ አሠልጣኝ ከቀድሞ ክለባቸው የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ የቴክኒክ ዳይሬክተር፣ የአሠልጣኝ እና የአዳዲስ ተጫዋቾች ትውውቅ መርሐ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ያከናወነ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው መርሐ ግብርም ያለፉትን ሁለት ዓመታት ቡድኑን ያሰለጠኑትን አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ክለቡ እውቅና ሰጥቷል።

በዚህም በአሁኑ ሰዓት የአዳማ ከተማ አሠልጣኝ የሆኑት ፋሲል ተካልኝ ምንም እንኳን በስፍራው ባይገኙን ለክለቡ ባበረከቱት አስተዋፅኦ የ500,000 ብር የገንዘብ ሽልማት በተወካያቸው አዳነ ግርማ አማካኝነት ተረክበዋል።