ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ድንቅ ብቃቱን ያሳየው የግብ ዘብ ሌላ ክለብ ለመቀላቀል ተስማምቷል።

ወደ ሀገራችን ከመምጣቱ በፊት ለሀገሩ ቶጎ ጎሚዶ ክለብ ቆይታ የነበረውን ቆይቶ አጠናቆ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በመምጣት ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ግብ ጠባቂው የሱፍ ሞሩ ለተጨማሪ ዓመት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ አሁን ወደ ሌላው የሀገራችን ክለብ ሸገር ከተማ ለመቀላቀል ተስማምቷል።
በቅርብ በተከናወኑ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ላይ በቶጎ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የነበረው ግብ ጠባቂው በሀገሩ ክለብ ጎሚዶ ቆይታ የነበረው ሲሆን ከዛ በፊትም በኮንጎው ሴንት ኤሎይ ሉፖፖ፣ ‘Future Stars Agoè’ ፣ ‘Jeunesse Club d’Agoè-Nyivé’ ፣ Dynamic Togolais Lomé’ መጫወት የቻለ ሲሆን ያለፈውን አንድ ዓመት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ሲሆን አሁን ሸገር ከተማን ለመቀላቀል ቅድመ ስምምነት መፈፀሙን አውቀናል።

