በቡናማዎቹ ቤት የሙከራ ጊዜ በማሳለፍ ላይ የቆየው ኮንጓዊ በቋሚነት ፈርሟል

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከሳምንታት በፊት ማቩንጉ ምቤሌ ጁንየር የተባለ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ዜግነት ላለው አማካይ የሙከራ ዕድል መስጠታቸው መግለፃችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ተጫዋቾ በተሰጠው የሙከራ ጊዜ ዋና አሰልጣኙ ማሳመኑን ተከትሎ በይፋ ቡድኑ እንደተቀላቀለ ክለቡ አስታውቋል። የ24 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ ተጫዋች በአማካይነት እንዲሁም በመስመር ተጫዋችነት መሰለፍ የሚችል ሲሆን ከዚህ ቀደም በዶን ቦስኮ እና ሴንት ኤሎይ ሉፖፖ በተባሉ ክለቦች መጫወት ችሏል።

