አንተነህ ተስፋዬ ዐፄዎቹን ተቀላቀለ

አንተነህ ተስፋዬ ዐፄዎቹን ተቀላቀለ

በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው ተከላካይ ወደ ፋሲል ከነማ አምርቷል

በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የሚመሩት እና ለአዲሱ ውድድር ዓመት ራሳቸውን ለማጠናከር በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ አድርገው ላለፉት ወራት በዝግጅት ላይ የቆዩት ፋሲል ከነማዎች አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው የመሀል ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬን የክረምቱ የዝውውር መስኮት የመጨረሻ ፈራሚያቸውን አድርገዋል።

አንተነህ ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ መቻል እንዲሁም ያለፈውን አንድ ዓመት በሽረ ምድረ ገነት መጫወቱ ይታወሳል።