ባለፈው ዓመት በዐፄዎቹ ቤት ቆይታ የነበረው አጥቂ ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ አምርቷል

10 ግቦች ካስቆጠረበት የተሳካው የ2017 የውድድር ዓመት በኋላ ወደ ፋሲል ከነማ አምርቶ በዐፄዎቹ ቤት የአንድ ዓመት ቆይታ የነበረው አጥቂው ያሬድ ብርሀኑ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሏል። ከዚ ቀደም በመቐለ 70 እንደርታ፣ ደደቢት፣ ወልድያ ከተማ፣ ወልዋሎ፣ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ መጫወት የቻለው አጥቂው ከክለብ እግር ኳስ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድንም መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርቷል።

