እዮብ አለማየሁ ወደ ወልዋሎ ተመልሷል

ወደ ወልዋሎ ለማምራት ተስማምቶ የቅድመ ስምምነት ከፈፀመ በኋላ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካመራ በኋላ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ዳግም ወደ ወልዋሎ ተመልሶ ከክለቡ ጋር እንዲቀጥል የተወሰነለት የፊት መስመር ተጫዋቹ እዮብ አለማየሁ በዛሬው ፌርማውን አኑሯል።
የአንድ ዓመት ውል የፈረመው ተጫዋቹ የቢጫዎቹን ስብስብ የተቀላቀለ ሲሆን በነገው ዕለት ልምምድ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

