የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ ዞን ወደ መገባደጃው ደርሷል፡፡ የዚህ ዞን ውድድር ሊጠናቀቅ 1 ሳምንት የቀረው ሲሆን በመጪው ረቡዕ በሚደረጉ ጨዋታዎችም ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
ከዚህ ዞን ወደ ማጠቃለያው ያለፉት 6 ቡድኖች የታወቁ በመሆኑ በመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች የሚጠበቀው የዞኑ ቻምፒዮን ማን ይሆናል የሚለው ነው፡፡
የ17ኛ ሳምንት ውጤቶች
ቅዳሜ ሰኔ 4 ቀን 2008
ደደቢት 3-1 ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ
ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-2 አዲስ አበባ ከተማ
እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-0 አፍሮ ፅዮን
ረቡዕ ሰኔ 8 ቀን 2008
ሐረር ሲቲ 2-0 ኤሌክትሪክ
መከላከያ 2-1 ኢትዮጵያ ቡና
የመጨረሻ ሳምንት ፕሮግራም
ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2008
05፡00 አፍሮ ፅዮን ከ ኢትዮጵያ ቡና (መድን ሜዳ ፣ ቃሊቲ)
እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2008
03፡00 ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከ ሐረር ሲቲ (መድን ሜዳ ፣ ቃሊቲ)
03፡00 መከላከያ ከ ደደቢት (አአ ስታድየም)
09፡00 አዲስ አበባ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ባንክ ሜዳ ፣ ሲኤምሲ)
ረቡዕ ሰኔ 15 ቀን 2008
10፡00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኤሌክትሪክ ሜዳ ፣ ጎፋ)
የማጠቃለያ ውድድር
-10 ክለቦች ይሳተፉበታል
-ከመካከለኛ ዞን 6 ፣ ከደቡብ-ምስራቅ ዞን 4 ክለቦች ይሳተፋሉ፡፡
-በአዳማ አስተናጋጅነት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል
ተሳታፊ ክለቦች
መካከለኛ ዞን ፡ ደደቢት ፣ ሐረር ሲቲ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መከላከያ ፣ አዲስ አበባ ከተማ
ደቡብ-ምስራቅ ዞን ፡ ሀዋሳ ከተማ (ቻምፒዮን) ፣ ሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ
