ዳሽን ቢራ ከ ሲዳማ ቡና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ዳሽን ቢራ 1-0 ሲዳማ ቡና
38′ ኤዶም ሆሶዎሮቪ


ተጠናቀቀ
ጨዋታው በዳሽን አሸናፊነት ቢጠናቀቅም ከመውረድ መትረፍ አልቻለም፡፡ ተጨዋቾቹ ላይ ጥልቅ የሆነ የሀዘን ስሜት ይታያል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ዳሽን
82′
አስራት መገርሳ ወጥቶ ደረጄ መንግስቱ ገብቷል፡፡

80′ አዲስ አባባ ስቴዲዮም ላይ ኤሌክትሪክ እየመራ በመሆኑ ውጤቱ እስካልተቀየረ ድረስ ዳሽን ከመውረድ አፋፍ ላይ ቆሟል፡፡

72′ አዲስ ግደይ የዳሽን ተከላካዮችን አተራምሶ ከርቀት የመታው ኳስ ለጥቂት በግቡ አናት ላይ ወጥቷል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
67′
አዲስ አለም ደበበ ገብቶ ወሰኑ ማዜ ወጥቷል፡፡

64′ አምሳሉ ጥላሁን እና የተሻ ግዛው የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

60′ በጣም የተቀዛቀዘና ፍላጎት የማይታይበት ጨዋታ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

አአ ስታድየም
ኤሌክትሪክ በፒተር ኑዋድኬ ጎል 1-0 እየመራ ይገኛል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የመጀመርያ ግማሽ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ጎልልል!!!! ዳሽን
38′ ኤዶም ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት አስቆጠረ፡፡

33′ ከቀኝ መስመር የተሻማውን ቅጣት ምት ኤዶም በግንባሩ ሞክሮ ለጥቂት ወጣ፡፡

27′ የጨዋታው እንቅስቃሴ በመሀል ሜዳ ላይ ብቻ የተገደበ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ቢጫ ካርድ
19′
አዲስ ግደይ ወደጎል ብቻውን በመግባት ላይ እያለ መላኩ ጎትቶ በማስቀረቱ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

14′ ጨዋታው ተሟሙቋል፡፡ ፀጋዬ በቀኝ መስመር ሰብሮ በመግባት የመታውን ኳስ ቢንያም እንደምንም አድኖታል፡፡

11′ ምንያህል ይመር ከ16:50 ውጭ አክርሮ የመታውን ኳስ ፍቅሩ እንደምንም አወጣበት፡፡

8′ ጨዋታው ተቀዛቅዞ ቢጀመርም ሁለቱም ቡድኖች ወደ ጨዋታው ለመግባት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በዳሽን አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የዳሽን ቢራ አሰላለፍ

1 ቢንያም ሀብታሙ

2 ኪዳኔ ተስፋዬ – 24 መላኩ ፈጠነ – 26 ያሬድ ባየህ – 21 አምሳሉ ጥላሁን

8 ምንያህል ይመር – 4 አስራት መገርሳ – 11 ኤርሚያስ ሃይሉ

25 መሃመድ ሸሪፍ ዲን – 9 ኤዶም ሆሶውሮቪ – 10 የተሻ ግዛው

ተጠባባቂዎች
31 ቴዎድሮስ ጌትነት
15 አሌክስ ተሰማ
19 ማይክ ቦሪስ
6 ደረጄ መንግስቱ
17 ብርሃኑ በላይ
12 አዲሱ አላሮ


የሲዳማ ቡና አሰላለፍ

1 ፍቅሩ ወዴሳ

19 ተመስገን ካስትሮ – 4 አንተነህ ተስፋዬ – 33 አወል አብደላ – 15 ሳውሬል ኦልሪሽ

22 ወሰኑ ማዜ – 5 ፍፁም ተፈሪ – 20 ሙሉአለም መስፍን – 14 አዲስ ግደይ – 25 ክፍሉ ኪአ

9 በረከት አዲሱ

ተጠባባቂዎች
89 አዱኛ ፀጋዬ
16 እምሻው ካሱ
6 አዲስአለም ደበበ
19 ዮሃንስ ዳንኤል
27 ላኪ ባሪለዱም ሳኒ
21 አንዱአለም ንጉሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *