አማኑኤል ተርፉ የግብጹን ክለብ ተቀላቀለ

አማኑኤል ተርፉ የግብጹን ክለብ ተቀላቀለ

ኢትዮጵያዊው የመሃል ተከላካይ የግብጹን ክለብ መቀላቀሉ ታውቋል።

ከ2010 ጀምሮ እስከ 2017 ድረስ በፈረሰኞቹ ቤት መጫወት የቻለው እና እየተሻሻሉ መጥተው ራሳቸውን ማሳየት ከቻሉት ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው አማኑኤል ተርፉ ከአሳዳጊ ክለቡ ጋር በመለያየት ወደ ግብጽ አምርቶ የተሳካ የሙከራ ጊዜን በማሳለፉ ለፔትሮጄት ፊርማውን አኑሯል።

ሁለት የሊግ እና አንድ የሲቲ ካፕ ዋንጫዎችን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያነሳው የመሃል ተከላካዩ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ተመርጦ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን ከዚህ በፊት ሽመልስ በቀለ ሲጫወትበት በነበረበት ፔትሮጄት ክለብ ለሁለት ዓመታት የሚቆይበትን ውል ፈርሟል።