አሰልጣኝ መሠረት ማኔን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው መቻል አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋች ኮንትራትን ደግሞ አድሷል።
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የተጠናቀቀውን ዓመት አምስተኛ ሆኖ መፈፀሙን ተከትሎ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተቋሙ ውጪ አዲስ አሰልጣኝ በማድረግ መሠረት ማኔን በዋና አሰልጣኝነት የሾመው መቻል የአራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ፊርማ ሲያገኝ የአንድ ነባርን ውል ደግሞ አራዝሟል።
ዕፀገነት ብዙነህ የአሰልጣኟን ፈለግ ተከትላ መቻል ደርሳለች። የቀድሞዋ የደደቢት ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አዳማ ከተማ እና ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታን ካደረገች በኋላ የመስመር ተከላካዩዋ መዳረሻዋ የአሰልጣኟን ፈለግ ተከትላ ወደ መቻል ተጉዛለች።
አጥቂዋ ትንቢት ሳሙኤልም የመቻል አዲሷ ተጫዋች ሆናለች። በድሬዳዋ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ ተከታታይ ሁለት ዓመታትን ካሳለፈች በኋላ የቀደመ አሰልጣኟን ጥሪ ተቀብላ መቻል ደርሳለች።
የግብ ዘቧ ቤቴልሔም ዮሐንስም መቻል ደርሳለች። በአዲስ አበባ ከተማ ፣ አርባምንጭ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ቆይታን በማድረግ ሦስተኛ ፈራሚ ሆና መቻል ደርሳለች። ሌላኛዋ ከአርባምንጭ ከተማ ከተገኘች በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጫወት የቻለችው የመሐል ተከላካዩዋ ድርሻዬ መንዛም ምርጫዋን መቻል አድርጋለች።
አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ በመቀላቀል ወደ ዝውውሩ የገባው ቡድኑ የአማካዩዋ ገነት ኃይሉን ውል ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት አድሶላታል።