የአብስራ ተስፋዬ ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል

የአብስራ ተስፋዬ ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል

በመቐለ 70 እንደርታ ዓመቱን ያሳለፈው የአማካይ መስመር ተጫዋች ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለማምራት ከጫፍ መድረሱ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ከተከፈተ በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ በገፍ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ባንመለከትም አንዳንድ ክለቦች የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ እንዲሁም አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ከቀናት በፊት ከአሠልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ጋር የተለያየው እና አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን በቦታው የሾመው መቻል ብሩክ ማርቆስን የግሉ ለማድረግ ስምምነት ላይ የደረሰ መሆኑን ዘገባ ያቀረብን ሲሆን አሁን ደግሞ ክለቡ ተጨማሪ የአማካይ መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ከጫፍ መድረሱን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

በዚህም በውድድር ዓመቱ በመቐለ 70 እንደርታ ያሳለፈው የቀድሞ የደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ አማካይ የአብስራ ተስፋዬ መቻልን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።

የአብስራ ያሳለፈበት መቐለ 70 እንደርታ ከካስ ጋር ያለውን የክስ ሂደትን በተመለከተ ጉዳዩ ዝውውሩ ላይ የሚፈጥረው ነገር ይኑሩ አይኑሩ እስካሁን ባይታወቅም ተጫዋቹና ክለቡ ግን መስማማታቸው ታውቋል።