ከግብፁ ክለብ ጋር በስምምነት የተለያየው ፈጣኑ አጥቂ በቅርቡ አዲስ ክለብ ይቀላቀላል።
ላለፈው አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከግብፁ ዜድ ጋር ቆይታ የነበረው እና ቀሪ ውል እያለው ከክለቡ ጋር በስምምነት የተለያየው የፊት መስመር ተጫዋቹ አቤል ያለው ወደ መቻል ለማምራት ከጫፍ ደርሷል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ የዝውውር መስኮት ላይ ከመቐለ 70 እንደርታ እና መቻል ጋር ካደረገው ድርድር በኋላ ጦሩን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ ዝውውሩ በአንዳንድ ምክንያቶች ሳይሳካ ከቀረ በኋላ አሁን ግን ከግብፁ ክለብ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ጦሩን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።
በቃሊቲ እግርኳስን የጀመረው አጥቂው ከዚህ ቀደም በሐረር ሲቲ፣ ደደቢት፣ ፋሲል ከነማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ዜድ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወቱ ሲታወስ አሁን ደግሞ ከአንድ ዓመት የስድስት ወር የግብፅ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ከጫፍ ደርሷል።